Mission and Vision
ተልዕኮ (Mission):
የሃገራችንን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሠረት በማድረግ፣ ጥራትንና ተገቢነትን የጠበቀ የሥልጠና አገልግሎት በማቅረብ በዕዉቀት፣ በክህሎትና በመልካም ሥነ ምግባር የታነጹ በክልሉ ዕድገትና ልማት እንዲመጣና ዴሞክራሲያዊ ባህል እንዲዳብር አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ የአንደኛ ደረጃ መምህራንን ማፍራት ፤
- ብቁ የሆኑ አሠልጣኝ መምህራንን በማሟላት ፣
- ትምህርትና ስልጠናን በቴክኖሎጂና በጥናትና ምርምር በማስደገፍ፣
- መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞችን በመጠቀም፣
- አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር እና የተገኘውን ሃብት በአግባቡ በመጠቀምጠንክሮ መስራት ነው።
ራዕይ (vision):
በ2017 ዓ.ም የኮሌጁ የማሰልጠን አቅም፤ጥራትና ደረጀው አድጎ ሁላንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ለልማት፤ለፍትህ ፤ለሰላምና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የጎላ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የሠለጠነ የሠው ኃይል በማፍራት በሀገር እቀፍ ደረጃ አርኣያነት ያለው የሥልጠና ማዕከልና ኮሌጁም ወደ ድግሪ ሥልጠና መርሃ-ግብር አድጎ /center of excellence/ ሆኖ ማየት ።